›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መጋቢት 04 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የስነ-ምግባር ግድፈት በፈጸሙ አምስት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና በአንድ ሬጅስትራር ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
ጉባኤው ከዚህ በፊት በነበሩ አመታት የተከማቹ የዲሲፕሊን ክሶችን እልባት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ሲሆን በሂደት ላይ ያሉ የክስ መዝገቦች እንደተጠበቁ ሆነው በሶስት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ እንደ ቅደም ተከተላቸው የቃል፤የጽሁፍና የአንድ ወር ደመወዝ በሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ አንዱ በነጻ የተሰናበቱ ሲሆን ሌላኛው የሁለት ወር ደመወዝ እንዲሁም አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡና በተጨማሪም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
Views 225